Fana: At a Speed of Life!

የሻሸመኔ ከተማ የወደፊት እጣ ፈንታ የሚወሰነው በዛሬዎቹ ነዋሪዎቿ ነው – የሻሻመኔ አባ ገዳዎች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሻሻመኔ አባ ገዳዎች ብሔርን ለይቶ ጥቃት የሚፈፅም እና ንብረት  ላይ ማንኛውንም ጉዳት የሚያደርስ ሰው ልጃችን አይደለም ሲሉ ውሳኔ አስተላለፉ።

አባ ገዳዎቹ የሻሸመኔ ከተማ የወደፊት እጣ ፈንታ የሚወሰነው በዛሬዎቹ ነዋሪዎቿ ነውም ብለዋል።

በከተማዋ የሰላም እና የእርቅ ኮንፈረንስ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል፤ መድረኩ ዛሬ እና ነገን ጨምሮ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል።

በኮንፈረንሱ ላይ ከምዕራብ አርሲ የተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ አባ ገዳዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ወጣቱ ልማት ላይ ትኩረት አድርጎ እንዲሰራ አባ ገዳዎቹ ጥሪ አቅርበዋል።

የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ አቶ ጉታ ላቾሬ በሻሻመኔ ከተማ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ የተለያዩ የንግድ እና ሌሎች ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱን አስታውሰዋል።

ለመልሶ ማቋቋም እስካሁን 42 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ያስታወሱ ሲሆን፤ 46 አመራሮች እና 42 የፖሊስ አባላት ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል።

በመልሶ ማቋቋም ሥራው 818 ቤቶች ጥገና ተደርጎላቸዋል።

ከተጠርጣሪዎች ውስጥ 280ዎቹ ላይ ክስ መመስረቱን፣ 441 የሚሆኑት በዋስ መለለቃቸው ተገልጿል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.