Fana: At a Speed of Life!

የሽሬ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች በህወሓት ቡድን የነበረው የዝምድና አሰራር ከዚህ በኋላ እንደማይቀጥል ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 22 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህወሓት ቡድን የነበረው የኔትወርክና የዝምድና አሰራር ከዚህ በኋላ እንዳይቀጥል በማድርግ ሕዝቡን በቅንነት ለማገልገል መዘጋጀታቸውን የሽሬ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ገለጹ፡፡
አመራሮቹ በህወሓት ጁንታ አድሏዊ አስተዳደር ተማርሮ የነበረውን የከተማውን ነዋሪ በቅንነትና ታማኝነት ለማገልገል መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
በሽሬ ከተማ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ከንቲባ በመሆን የተመረጡት መምህር ሐጎስ በርሄ ህዝባዊ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
“ከአገር ሽማግሌዎች፣ ከወጣቶችና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በመሆን በከተማዋ ሰላም እንዲሰፍን፣ ማህበራዊ አገልግሎቶች እንዲሳለጡና ልማት እንዲከናወን እሰራለሁ” ብለዋል።
የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ሆነው የተመረጡት ኢንጂነር ጀሚል ሙሐመድ በበኩላቸው÷ ሕዝብ የጣለባቸውን ሃላፊነት በብቃት ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል።
በከተማው ጊዜያዊ አስተዳደር መቋቋሙ ለሕዝቡ መረጋጋት እንደሚያመጣ ጠቁመው÷ ሰላም ለማረጋገጥ ሂደትም ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
በከተማው የአቅም ግንባታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው የተመረጡት መምህርት ንግሥቲ ፋንታሁንም ህዝቡን በቅንነትና ታማኝነት ለማገልገል መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል።
የከተማው ነዋሪዎች ከጎናቸው በመቆም ድጋፍና እገዛ እንዲያደርጉላቸውም አመራሮቹ ጠይቀው ቀደም ሲል በህወሃት ጁንታ ዘመን የነበረው በመተዋወቅ፣ በዝምድናና በኔትወርክ መስራት እንደማይደገም አረጋግጠዋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው የተሾሙት ዶክተር ሙሉ ነጋ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ ህዝቡን በማወያየት ላይ እንደሚገኙ ኢዜአ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.