Fana: At a Speed of Life!

የቀይ ባህር ጂኦ ፖለቲካዊ ሁኔታና የትብብር መማክርት ምስረታ ሊቋቋም መታሰቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀይ ባህር ጂኦ ፖለቲካዊ ሁኔታና የትብብር መማክርት ምስረታ ሊቋቋም መታሰቡ ተገለጸ፡፡

ይህ የተባለው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ለሦስት ተከታታይ ቀናት ባካሀየዱቴ የምክክር መድረክ ላይ ነው፡፡

በምክክር መድረኩ ፓርላማው የዲፕሎማሲ አውታር ሊሆን እንደሚገባው ተጠቁሟል፡፡

በውይይት መድረኩ አምባሳደር ሻሜቦ ፈታሞ ቀይ ባህር በዓለም ንግድ ልውውጥ ወሳኝ ድርሻ ያላት መሆኗን ጠቅሰው፤ በቀጠናው ያሉ ሃገራት በፖለቲካ እና በኢኮኖሚ መስኮች የተሻሉ ለውጦች እያደረጉ መሆናቸውንም አመላክተዋል፡፡

አምባሳደሩ የቀይ ባህር ጂኦ ፖለቲካዊ ሁኔታና የትብብር መማክርት ምስረታ ሊቋቋም መታሰቡን ጠቅሰዋል፡፡

በምክክር መድረኩ የተገኙ የምክር ቤት አባላት ቀይ ባህርን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት ግብጽ እየተከተለች ያለችውን የጥፋት መንገድ በመረዳት የአገሪቱን ህልውና ለማስቀጠል ከጎረቤት ሃገራት ጋር ያለትን ግንኙነት ማጠናከር እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

እያንዳንዱ ዜጋም በሄደበት ሃገርም ሆነ በሚሰራበት ተቋም እንደ ዲፕሎማት በመስራት ተጽእኖ ፈጣሪ ሊሆን እንደሚገባ የጠቆሙት የምክር ቤቱ አባላት በፓርላማ ዲፕሎማሲ ላይ በትኩረት በመስራት ፓርላማውን የዲፕሎማሲ አውታር ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

የፓርላማ ዲፕሎማሲ የምክር ቤቶች የውጭ ግንኙነት ስራ የሃገራችንን አቋም ለማንጸባረቅ፣ የአሰራር ልምዶችን ለመቅሰም፣ የሃገሪቱን ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚዊ እንቅስቃሴ ለዓለም ህብረተሰብ ለማሳወቅ ብሎም ዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ ለማግኘት እንደሚያገለግል በምክክር መድረኩ ተመላክቷል፡፡

የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የተካሄደውን የምክክር መድረክ አስፈላጊነት በገለጹበት ወቅት፤ መድረኩ ኢትዮጵያ ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ የሚያስቃኝ በመሆኑ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ነው ብለዋል፡፡

ዶክተር ነገሪ አክለውም ውስጣዊ አንድነታችንን እና ከጎረቤት ሃገራት ጋር ያለንን ግንኙነት በማጠናከር ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት ትኩረታችን ግድባችንን በማጠናቀቅ ላይ ሊሆን እንደሚገባ ማስገንዘባችውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.