Fana: At a Speed of Life!

የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በመዲናዋ ያስገነባውን የዳቦና ዱቄት ፋብሪካ አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ6ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያስገነባውን የዳቦና ዱቄት ፋብሪካ አስመርቋል፡፡

በቀን 1 ሚሊየን ዳቦ የሚያመርተው የዳቦና ዱቄት ፋብሪካው 217 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበት ነው፡፡

ለ450 ሰዎች የስራ እድል የሚፈጥረው ይህ ግዙፍ የዳቦ ፋብሪካ በቀን 72 ቶን ዱቄት ጎን ለጎን ያመርታልም ተብሎለታል፡፡

የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ያስገነባው የዳቦና ዱቄት ፋብሪካው የምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ተገኝተው ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አስረክበዋል፡፡

የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት በቀጣይ በአስር ዋና ዋና ከተሞች ለሚገነባው የዳቦና ዱቄት ፋብሪካ ግንባታ ሂደት ላይ ይገኛል፡፡

በነዚህ ከተሞች የሚገነቡት ፋብሪካዎች እያንዳንዳቸው በቀን 400 ኩንታል ዱቄት የማምረትና 300ሺህ ዳቦ የመጋገር አቅም እንደሚኖራቸው ተገልጿል፡፡

በፍሬህይወት ሰፊው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.