Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞዋ አምባሳደር ቆንጅት ስነጊዮርጊስ የ2020 የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሽልማት ሊበረከትላቸው ነው

አዲስ አበባ ፣ህዳር 22 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያዊቷ አንጋፋ ዲፕሎማት አምባሳደር ቆንጅት ስነጊዮርጊስ የ2020 የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሽልማት ሊበረከትላቸው ነው።
የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደሯ የዘንድሮው ሽልማት ከሚበረከትላቸው ግለሰቦች መካከል አንደኛዋ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡
ሽልማቱ በጃፓን እና በሌሎች ሀገራት መካከል ያለው ወዳጅነትና ትብብር እንዲስፋፋ የላቀ ስራ ለሰሩ ግለሰቦች እና ቡድኖች የሚሰጥ መሆኑ ተመላክቷል።
አምባሳደሯም በጃፓን እና በአፍሪካ መካከል የጋራ መግባባት እንዲኖር ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅኦ ሽልማቱ እንደሚበረከትላቸው በአፍሪካ የጃፓን መልዕክተሻ አስታውቋል፡፡
በተለይም አምባሳደሯ በአፍሪካ ህብረት እና ዓለም አቀፍ የአፍሪካ ልማት ጉባኤ የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ በነበሩበት ወቅት ስኬተማ ስራ መስራታቸው ተጠቅሷል፡፡
አምባሳደር ቆንጂት በአምባሳደርነት፣ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ምክር ቤት ሰብሳቢ እና በቀድሞው የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚ ኮሚሽን ለአፍሪካ ቋሚ መልዕክተኛ ሆነው አገልግለዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.