Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞው የኒጀር ፕሬዚዳንት ማማዱ ታንጃ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የኒጀር ፕሬዚዳንት ማማዱ ታንጃ በ82 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰማ፡፡

ማማዱ ታንጃ ከፈረንጆቹ 1999 እስከ 2010 በስልጣን መቆየታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ከሁለት ጊዜ በላይ በስልጣን ለመቆየት ከሞከሩ በኋላ ግን በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን መነሳታቸው ይታወሳል፡፡

ከስልጣን ከተነሱ በኋላም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ወህኒ ከወረዱ አንድ ዓመት በኋላ ነጻ ወጥተውም ነበር ፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.