Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው ያገለገሉት አቶ ንዋይ ገብረአብ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ለረዥም ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የየቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው ያገለገሉት አቶ ንዋይ ገብረአብ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

አቶ ንዋይ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ከ1970ዎቹ ጀምሮ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና በፕላን ኮሚሽን ውስጥም ለረዥም ዓመታት አገልግለዋል።

አቶ ንዋይ ከኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪነታቸው ባለፈ የኢትዮጵያ የልማት ጥናት ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል።

በተባበሩት መንግስታት የተለያዩ ድርጅቶች ውስጥም በአማካሪነት ሰርተዋል።

አቶ ንዋይ ከአዲስ አበባ እና ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.