Fana: At a Speed of Life!

የቀጣይ ስድስት ወራት የኤች አይ ቪ ተጋላጭ ማህበረሰብ የምርመራ ዘመቻ የንቅናቄ መርሀ ግብር በድሬዳዋ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14 ፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ አስተዳደር የቀጣይ ስድስት ወራት የኤች አይ ቪ ተጋላጭ ማህበረሰብ የምርመራ ዘመቻ የንቅናቄ መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡

እንደ ሀገር የተጀመረውን የኤች አይ ቪ ኤድስ ተጋላጭ ማህበረሰቦችን ምርመራ እና መፍትሄ ማመቻቸትና የንቅናቄ አቅጣጫ መርሀ ግብር የሚደግፍ መድረክ ነው አስተዳደሩ ያካሄደው፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዩሱፍ ሰይድ እንደተናገሩት የኤች አይ ቪ ኤድስ ታማሚዎች እንደ ሀገር ቁጥራቸው እየጨመረ መጥቷል፡፡

ስለሆነም ትኩረት የሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመለየት አገልግሎት ለመስጠትና ለመከታተል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን ገልፀዋል፡፡

ቀደም ባሉት ጊዜያት ታማሚዎችን ወደ ህክምና በማምጣት አገልግሎቱን እንዲያገኙ ማድረግ ላይ ክፍተት እንደነበረም አስታውሰዋል፡፡

በዚህ ዘመቻ ላይ ግን ይህንን ችግር በመቅረፍ የተለዩ ማህበረሰቦችን በመመርመር በሽታው በውስጣቸው የተገኘባቸውን ታማሚዎች አገልግሎቱን በአግባቡ እንዲያገኙ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል፡፡

የዘመቻው ስራ በየሳምንቱ የሚፈተሸና እንደየአስፈላጊነቱ የሚከለስ ይሆናልም ነው ያሉት፡፡

በመድረኩ እንደተገለፀው ኤች አይ ቪ ኤድስ በሚቀጥሉት ጊዜያት በማህበረሰቡ ውስጥ ስጋት ሆኖ እንዳይቀጥል በጤናው ዘርፍ ያሉ ባለሙያዎች ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይገባቸዋል ተብሏል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.