Fana: At a Speed of Life!

የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ዜጎች በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቆላማና አካባቢዎች ፕሮጀክት በአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና፣ አርብቶ አደርና አካባቢ ጥበቃ ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ቀርቧል፡፡

በዚህ ወቅት በሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና አርብቶ አደር ጉዳዮች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ስዩም መስፍን ፕሮጀክቱ በአካባቢው የሚገኙ ማህበረሰቦችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ነው ብለዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በአፋር፣ ሶማሌ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋንቤላ ፣በኦሮሚያና በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች ክልሎች የሚገኙ አርብቶና ከፊል አርሶ አደሮችን ላይ የሚሰራ ነው ተብሏል ፡፡

ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን ምርታማነትን ሊጨምሩ የሚችሉ ጥናቶችን በማካሄድ ማህበረሰቡ የተሻሉ ዝርያዎችን እንዲያረባ ማድረግ እና ምርታማነትን በማሳደግ ጠንካራ የገበያ ትስስር መፍጠር ፕሮጀክቱ በዋናነት እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

ወጣቶችን በማደራጀት የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ወጣቱን ወደ ስራ በማሰማራት የልማቱ ተጠቃሚ ማድረግ የፕሮጀክቱ አንዱ የስራ አካል እንደሆነ ነው በውይይት መድረኩ የተገፀው ፡፡

የግብርና አርብቶ አደርና አካባቢ ጥበቃ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሰቢ ወይዘሮ አልማዝ መሰለ በቀጣይ ፕሮጀክቱ የሚያከናውናቸው ተግባራት ዘላቂነትና ቀጣይነት ያላቸው ሊሆኑ ይገባል በማለት ገልፀዋል፡፡

ፕሮጀክቱ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርግሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 50 በመቶ ሴቶች እንዲሁም 20 በመቶ ወጣቶች መሆናቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.