Fana: At a Speed of Life!

የበረሃ አንበጣ መንጋ በአፋር እና አማራ ክልል መከሰቱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የበረሃ አንበጣ መንጋ በአፋር እና በአማራ ክልል መከሰቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በኢትዮጵያ የበረሃ አንበጣ ከተከሰተባቸው ሌሎች ክልሎች ባለፈ በአፋር እና በአማራ ክልሎችም ከጂቡቲና ከሶማሊያ የገባ መንጋ መታየቱ ተገልጿል፡፡
የግብርና ሚኒስቴርም የበረሃ አንበጣ መንጋ በተከሰተባቸው ቦታዎች በ13 አውሮፕላኖች የኬሚካል ርጭት እያከናወነ መሆኑ ታውቋል፡፡
አሁን ላይ በተከሰተባቸው ሁለቱ ክልሎችም አውሮፕላኖችን በማሰማራት የኬሚካል ርጭቱን ለመጀመር እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ሚኒስቴሩ የበረሃ አንበጣን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚደረግ ጥረት ውስጥ በቀን እሰከ 8 ሺህ ሊትር ኬሚካልን በመጠቀም ርጭት እያከናወ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡
በሃይማኖት እያሱ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.