Fana: At a Speed of Life!

የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እንቅስቃሴ የአብሮነታችን ማሳያ ነው – ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 27 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በከተማዋ የአቅመ ደካማ ነዋሪዎችን ቤት ማደስ እና ሌሎች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተግባራት የአብሮነታችን ማሳያ መሆናቸውን ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ምክትል  ከንቲባዋ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በጉለሌ ክፍለከተማ አስተባባሪነት በክፍለ ከተማው እና በሱሉልታ ከተማ  በበጎ ፍቃደኞች ለአቅመ ደካማ ነዋሪዎች የታደሱ ቤቶችን  በዛሬው ዕለት አስረክበዋል።

ልማት ሁሉንም ማህበረሰብ አካታች መሆን አለበት ያሉት ከንቲባዋ መሰል የወሰን ተሻጋሪ እና ሌሎች የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች  የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን የሚያጠናክሩ በመሆኑ በይበልጥ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተናግረዋል።

በዓሉን በማስመልከት  የአቅመ ደካማ የነዋሪዎች ቤት የማደስ እና የተለያዩ ድጋፍ እንዲደረግ  አስተዋጽዖ ላበረከቱ በጎ ፍቃደኞች፣ ነዋሪዎች እና አመራሮች ሁሉ ምክትል ከንቲባዋ ምስጋና አቅርበዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጸሚ አቶ አባወይ ዮሐንስ የገና በዓልን በማስመልከት  በክፍለ ከተማው በርካታ ተግባራት መከናወኑን ገልጸዋል፡፡

በወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የሱሉልታ ከተማን ጨምሮ 73 የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት፣ለአቅመ ደካማ ነዋሪዎች፣ ለፌደራል እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት 39 የእርድ ሰንጋ በሬዎች፣ 114 በጎች እና ግምታቸው 3 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር  የተለያዩ አልሚ ምግቦችና አልባሳት ድጋፍ መደረጉን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተርያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.