Fana: At a Speed of Life!

የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አመራሮች በከተማዋ በሚገኙ ሆቴሎች ላይ ድንገተኛ ጉብኝትና ፍተሻ አካሄዱ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 27፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አመራሮች ከአዲስ አበባ የሆቴል ባለቤቶች ማህበር ጋር በመሆን በከተማዋ በሚገኙ ሆቴሎች ላይ ድንገተኛ ጉብኝትና ፍተሻ ማካሄዳቸው ተገለጸ፡፡
ጉብኝቱ የተካሄደው ሆቴሎች ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ እየወሰዱ ያለውን ጥንቃቄ ለመፈተሽ ነው ተብሏል፡፡
ጉብኝቱና ፍተሻው ዛሬ በካዛንቺስ እና ቦሌ አካባቢ በሚገኙ ሆቴሎች መካሄዱም ነው የተገለጸው፡፡
በኢፌዲሪ ባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው የተመራው ቡድን÷ የሆቴል ተገልጋዮችን አቀማመጥና ርቀት አጠባበቅ፣ የሆቴሎችን የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ አቅርቦት፣ በአንድ ስፍራ ላይ የሚከማቹ ሰዎች ብዛት እና መሰል ጥንቃቄዎችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል ነው የተባለው፡፡
በዚህም አብዛኞቹ ሆቴሎች በጥሩ ጥንቃቄ ላይ መሆናቸውንና አልፎ አልፎ ግን ሰዎች ተቀራርበው የተቀመጡባቸውና የጥንቃቄ ቁሳቁስ የማይጠቀሙ ሰራተኞች ያሉባቸውን ሆቴሎች ማግኘታቸውም ተገልጿል፡፡
ሆቴሌቹ የጥንቃቄ ጉድለት የታየባቸውን ነገሮች እንዲያስተካክሉ መነገሩን ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.