Fana: At a Speed of Life!

የቤልጅየም ም/ጠ/ሚ እና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለአቶ ደመቀ መኮንን የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት ላኩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፖላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዚቢግናዉ ራዬና የቤልጅየም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሶፊያ ዊልሚስ ለአቶ ደመቀ መኮንን የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላለፉ፡፡

ሶፊያ ዊልሚስ÷ አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጣቸው ባስተላለፉት የደስታ መልዕክት አዲሱ መንግስት በሁለቱ አገራት መካከል ያለዉን ወዳጅነት ለማስቀጠል በአለም አቀፍ፤ ቀጠናዊ እና በአካባቢው ጉዳዮች ላይ በጋራ እንሰራለን ብለዋል።

ቤልጅየም ኢትዮጵያ በሚገጥማት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ወዳጅነቷን አጠናክራ እንደምትቀጥልም በደስታ መግለጫው አስፍረዋል።

በተመሳሳይም የፖላንድ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዚቢግናዉ ራዬ ባስተላለፉት መልዕክት ÷ፖላንድ ከሳህራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት ለምታደርገዉ ግንኙነት ኢትዮጵያ ዋና መሸጋገሪያ በመሆን እና ለአፍሪካ ቀንድ ዋና የፖለቲካ ማዕከል በመሆኗ በሁለቱ አገራት ያለዉን ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ እንሰራለን ብለዋል።

በደስታ መግለጫው ለኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት የቆየ ወዳጅነትን መጠናከር በተለያዩ ዘርፎች ፖላንድ በትብብር እንደምትሰራ ገልፀዋል ።

የሁለቱ ሀገሮች መንግስታት ለኢትዮጵያ ህዝብ ልማት፣ ብልፅግና እድገት ያላቸዉን መልካም ምኞት መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.