Fana: At a Speed of Life!

የቤት ውስጥ የንፅህና መጠበቂያ ምርቶች ጨቅላ ህፃናትን ለአስም እንደሚያጋልጡ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህፃናት ልጆችን ደህንነቱ በተጠበቀ አካባቢ ማሳደግ ዋነኛው የቤተሰብ አላማ እና ፍላጎት ነው።

ልጆች በጉንፋን እና ሌሎች ተመሳሳይ የጤና ችግሮች እንዳይጋለጡ የቤት ውስጥ የንፅህና መጠበቂያዎችን ሲጠቀሙ ይስተዋል።

ሆኖም በቤት ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ የንፅህና መጠበቂያ ምርቶች የህፃናትን ጤና ለአደጋ እንደሚያጋልጡ አንድ ጥናት ይፋ አድርጓል።

የተወሰኑ የፅዳት መጠበቂያ ምርቶች የህጻናትን ከሳንባ ጋር ለተያያዙ በተለይም የአስም እና ተመሳይይ የጤና ችግሮች ተጋላጭነት ከፍ እንደሚያደርጉትም ጥናቱ ያመላከተው።

ጥናቱ ጨቅላ ህፃናቱ በእነዚህ የንፅህና መጠበቂያዎች ሳቢያ በአስም ይጠቃሉም ነው ያለው።

የጥናቱ መሪ ዶክተር ቲም ታካሮ የንፅህና መጠበቂያ ምርቶች ለፅዳት አስፈላጊ መሆናቸውን በመግለፅ ሆኖም በህጻናት ጤና ላይ ተፅዕኖ እንዳለው ህብረተሰቡ ሊያውቅ ይገባል ብለዋል።

የጥናት ቡድኑ ከተወለዱ እስከ አራት ወራት ውስጥ ለንጽህና መጠበቂያ ምርቶች ተጋላጭ የሆኑ የ2 ሺህ ህፃናትን ቤተሰቦች መረጃ ተጠቅሟል።

በጥናቱ ከተሳተፉት ውስጥ ከ3 እስከ 4 ዓመታቸው ድረስ በአካባቢያቸው ለሲጋራ ጭስ ያልተጋለጡ እና 70 በመቶ የሚሆኑት የህፃናት ቤተሰቦች የአስም ታሪክ የሌለባቸው ናቸው።

በዚህም ከፍ ባለ ሁኔታ በቤት ውስጥ የንፅህና መጠበቂያ ምርቶችን የሚጠቀሙ ቤተሰቦች ውስጥ የሚገኙ ጨቅላ ህፃናት በ3ኛ ዓመታቸው ላይ ለአስምና ተያያዥ ችግሮች እንደሚጋለጡ በጥናቱ ተረጋጧል።

የተለመዱት የንፅሃና መጠበቂያዎችም የእቃ ማጠቢያ ሳሙና፣ ኦሞ፣ የመስታወት ማፅጃ እና የልብስ ሳሙና ናቸው ተብሏል።

ምንጭ፡-healthline.com

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.