Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ክልል ምክር ቤት ከ5 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አፀደቀ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ለ2014 በጀት ዓመት ከ5 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አጸደቀ፡፡
የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ የሥራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ጉባዔውን የተለያዩ የማሻሻያ አዋጆችን በማጽደቅ ተጠናቋል፡፡
በቀረበው የበጀት ረቂቅ ላይ የተወያየው ምክር ቤቱ የ2014 አጠቃላይ የክልሉ በጀት 5 ቢሊየን 890 ሚሊየን 442 ሺህ 89 ብር አድርጎ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
ለበጀት ዓመቱ እንዲውል ከተያዘው በጀት ውስጥ 1 ቢሊየን 855 ሚሊየን 951 ሺህ 147 ብር በክልሉ ከሚሰበሰብ ገቢ የሚሸፈን ሲሆን፣ 3 ቢሊየን 542 ሚሊየን 958 ሺህ 540 የሚሆነው ከፌዴራል መንግስት በድጎማ፣ ቀሪው ደግሞ ከተለያዩ ተቋማት የውስጥ ገቢ፣ ከዘላቂ ልማት ግቦች ማሳኪያ እንዲሁም ከውጪ ከሚገኝ ዕርዳታ የሚገኝ የሚሸፈን ነው ተብሏል፡፡
በምክር ቤቱ ከጸደቀው አጠቃላይ በጀት ውስጥ 219 ሚሊየን 600 ሺህ ብር የሚሆነው ለዘላቂ ልማት ግቦች ማሳኪያ የሚውል መሆኑም ተገልጿል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት ለበጀት ዓመቱ ስራ ላይ እንዲውል የጸደቀው በጀት፣ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ በኩል ለታለመለት ዓላማ እንዲውል አስፈላጊውን ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ምክር ቤቱ በ2ኛ ቀን የጉባዔ ውሎው የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2013 ዓ.ም ዓመታዊ አፈጻጸም በማድመጥ ከተወያየ በኋላ መርምሮ አጽድቋል፡፡
ከዚህ ባለፈም የክልሉ ውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የማሻሻያ አዋጅን መርምሮ በማጽደቅ 12ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማጠናቁን ከክልሉ ኮሙዩኚኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.