Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልና የሱዳን የብሉ ናይል ግዛት አስተዳዳር የምክክር መድረክ በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልና የሱዳን ሪፐብሊክ የብሉ ናይል ግዛት አስተዳዳር የሁለትዮሽ የጋራ የምክክር መድረክ በአሶሳ ከተማ በመካሄድ ላይ ይግኛል።

የብሉናይል ግዛት ፕሬዚዳንት አብዱረሃማን ኑርዳይም በዛሬው እለት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የገቡ ሲሆን፥ በኩርሙክ ወረዳ በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች  አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልና የሱዳን ሪፐብሊክ የብሉ ናይል ግዛት አስተዳዳር የሁለትዮሽ የጋራ የምክክር መድረክበኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን ግንኙነት ለማስጀመር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህም ባለፈ በሁለትዮሽ የጋራ የምክክር መድረክ የጋራ የልማት ኮሚሽን ስራ አፈፃፀም ግምገማ፣ የሰላምና የፀጥታ እንዲሁም በሌሎችም የጋራ ጉዳዮች ላይ የሚመክር መሆኑም ታውቋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በምክክር መድረኩ፥ በሁለትዮሽ የጋራ የልማት ኮሚሽን በተሰሩ ስራዎች በዋናነት በአጎራባች አካባቢዎች የሚኖሩ ህዝቦች በሰላምና በፀጥታ ዙሪያ ከፍተኛ ስራ መሰራቱን ገልፀዋል።

የብሉናይል ግዛት ፕሬዚዳንት አብዱረሃማን ኑርዳይም በበኩላቸው፥ የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከኢትዮጵያዊያን አልፎ ለጎረቤት ሱዳናዊያን የሚያበረክተው አስተዋፅኦ የላቀ በመሆኑ አስታውቀዋል።

ስለዚህም በሁሉም ዘርፎች የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያበረክቱ መግለፃቸውን የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘገባ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.