Fana: At a Speed of Life!

የብሄራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ ልማት አገልግሎት በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን በኮምቦልቻ ከተማ የተመደቡ የብሄራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ ልማት አገልግሎት በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ከቀበሌ አመራሮችና ከአካባቢው ወጣቶች ጋር በመሆን ለአቅመ ደካሞች ድጋ ማድረጋቸውን ሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የድጋፉ ዓይትም ማካሮኒ፣ ፓስታ፣ ጤፍ ሌሎችም የምግብ እህሎች መሆናቸው ነው የተገለፀ ሲሆን÷ ከቀበሌ ነዋሪዎችና ነጋዴዎች የተሰበሰበ ነው ተብሏ፡፡
ድጋፉም ለ73 አቅመ ደካሞች መበርከቱን ከሰላም ሚኒስቴር ያኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የከተማ አስተዳድሩም በጎ ፈቃደኛ ወጣቶቹ ላደረጉት የበጎነት ተግባር ምስጋና አቅርቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.