Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ የ2013 ዓ.ም አፈጻጸምን ገመገመ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ የ2013 ዓ.ም አፈጻጸምን ገመገመ ፡፡
ሊጉ “እኩልነትና ህብረ ብሄራዊ አንድነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል 15ኛውን የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀንን በሸራተን አዲስ አክብሯል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ ሲቶች ሊግ ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መሰረት መስቀሌ በሃገሪቱ የሚገነባው ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሰው ልጆችን ተደማሪ ፍላጎት ማዕከል ያደረገ እንዲሆን ጥረት መደረጉን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም የዴሞክራሲ ይዘትንም ሆነ ሂደትን ታሳቢ ያደረገ ሁሉን የሚያሳትፍ እንዲሆን ብልጽግና ፓርቲ ጥረት ማድረጉንም ነው የተናገሩት፡፡
ወይዘሮ መሠረት አያይዘውም የብልጽግና ሴቶች ሊግ የአገር መከላከያ ሠራዊት የሕወሓት ጁንታ ላይ እየወሰደ ያለውን ሕግ የማስከበር እርምጃ ለመደገፍ እና ለማበረታታት ከ35 ሚሊየን ብር በላይ በገንዘብ እና በዓይነት ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል።
በተጨማሪም “የዓባይ ጉዳይ የህልውና ጉዳይ ነው! ግድቡ የኔ ነው!” በሚል መነቃቃት ባለፉት ወራት ከ16 ሚሊየን ብር በላይ የቦንድ ግዥ በሴቶች መፈጸሙን የብልጽግና ሴቶች ሊግ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መሠረት መስቀሌ ተናግረዋል።
በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ መንግስት ህግ ለማስከበር በወሰደው እርምጃ ለተሰው የሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የህሊና ጸሎት መደረጉን ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.