Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ በአዲስ አበባ ደረጃ የሚወዳደሩ ዕጩዎቹን አስተዋወቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ለስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ በአዲስ አበባ ደረጃ ለህዝብ ተወካዮችና ለአዲስ አበባ ምክር ቤት የሚወዳደሩ ዕጩዎቹን በሸራተን አዲስ አስተዋወቀ።

ፓርቲው 23 ዕጩዎችን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቅረቡን አስታውቋል፡፡

ከዚህ ባለፈም 138 ዕጩዎች ለአዲስ አበባ ምክር ቤት ማቅረቡን ገልጿል።

ከእጩዎቹ ውስጥ 50 በመቶ ሴቶች ናቸው ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ ብልጽግና ፓርቲ ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን የመፍጠር መርህን ይዞ እየሠራ ነው ብለዋል።

ፓርቲው ከተወዳዳሪነት በተጨማሪ እንደመንግሥት ምርጫው ፍትሐዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የማድረግ ተዓማኒነቱን የማረጋገጥና አርዓያ ሆኖ የመገኘት ሃላፊነት እንዳለበትም ገልጸዋል፡፡

የከተማ አሰተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ መለስ ዓለሙ የዴሞክራሲ ተቋማት ገለልተኛ ሆነው ምርጫውን ለማስፈፀም እየሠሩ ስለሆነ መደገፍ ይገባል ብለዋል።

ለእጩነት የተመረጡ ተወዳዳሪዎች የፓርቲውን ሥነ ምግባርና መራጩን ያከበረ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.