Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በጋምቤላ ከተማ የተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በጋምቤላ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማትን ጎብኝተዋል።
በጉብኝት መርሐ ግብሩ የተሳተፉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ፥ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።
በተለይም የክልሉ ብዙሃን መገናኛ አገልግሎት እያከናወነ ያለው ተግባር ለሌሎች አርዓያ መሆን የሚችል እንደሆነ አስታውቀዋል።
በአንድነቱ የጠነከረ ባለሙያ ከፈጠርንና የበሰለ አመራር መስጠት ከቻልን ከምንመኘው ብልፅግና ላይ መድረስ እንደምንችል የማስፋፊያ ህንፃ ግንባታው ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።
አመራሮች የአገልጋይነት ባህሪን በመላበስ ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ከመፍታት ጎን ለጎን የተመደባችሁበት የስራ አካባቢ ለሰራተኞችና ለተገልጋዩ ህዝብ ምቹና ፅዱ ማድረግ ይጠበቅባችኋል ነው ያሉት።
በጉብኝታቸው የክልሉ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ እያከናወነ ያለውን የቢሮ እድሳት እንዲሁም በጋምቤላ ከተማ ያሉ የዱቄት ፋብሪካዎችና ሌሎች ተቋማት ተጎብኝተዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.