Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ለመከላከያ ሰራዊት ያሰባሰበውን 10 ሚሊየን ብር አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ የመከላከያ ሰራዊትን ለመደገፍና ለማበረታታት ከኢትዮጵያ ወጣቶች ያሰባሰበውን 10 ሚሊየን ብር በመከላከያ ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት አስረክቧል።

ድጋፉን የተረከቡት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻልና ብርሀኑ ጁላ ባስተላለፉት መልዕክት፥ የኢትዮጵያ ወጣቶች ጀግኖችና አገር ጠባቂዎች ናቸው ብለዋል፡፡

ወጣቶች መከላከያ ሰራዊትን ከመደገፍ በተጨማሪ በግንባር በመሰለፍ ለአገራቸው መስዋዕት እየሆኑ ነው ሲሉም አክለዋል።

ሁሉም የሚኖረው አገር የሚጠብቅ መከላከያ በመኖሩ ነው ያሉት ኢታማዦሩ ሹሙ፥ ኢትዮጵያዊያን አንድነታቸውን በማስጠበቅ የመከላከያ ሰራዊትን ማጠናከር ይገባቸዋ ብለዋል።

በመቶ ለወገኔ ንቅናቄ የተሰበሰበ ገንዘብ ለመከላከያ ሰራዊት ያስረከቡት በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የፓለቲካ ፓርቲዎች ማስተባበሪያ ዘርፍ ሃላፊ ዶክተር ዓለሙ ስሜ በበኩላቸው፥ ወጣቶች አገራቸውን በመጠበቅ አለኝታነታቸውን በተግባር አሳይተዋል ማለታቸውን ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.