Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ውይይት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ሲያካሂድ የነበረውን ውይይት የተለያዩ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ አጠናቋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራትን በደብረ ብርሃን ከተማ ባካሄደው ውይይት የገመገመ ሲሆን÷ ሊጉ በየቀጣይ የሚያካሂደውን ጉባኤ አስመልክቶ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

የሊጉ ማዕከላዊ ኮሚቴ የቀጣዩን ጉባኤ ጊዜ ለመወሰን ውይይት ካካሄደ በኋላ ከመስከረም 25 እስከ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ባለው እንዲካሄድ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

በተመሳሳይ የብልፅግና ፖርቲ የወጣቶች ሊግ የ2014 አረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ማስጀመሪያና መርሐ ግብር በደብረብርሃን ከተማ አስጀምሯል፡፡

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የደብረ ብርሀን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ካሳሁን እንቢአለ÷ ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት፤ ወጣቶች ለኢትዮጵያ በአንድነት መቆም ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

ሊከፋፍሉን የሚፈልጉ የውጭም የውስጥም ባንዳዎች ሊያሸብሩን ቢፈልጉ በወጀቡ ሳንናወጥ የወደፊቷን ኢትዮጵያን ከፍ ለማድረግ እጅ ለእጅ መያያዝ አለብን ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በሰለጠነ መንገድ ችግርን መፍታት መለመድ አለበት ያሉት ከንቲባው÷ የውጭ ጠላቶቻችን የሚፈትኑን የፈጣሪ ፀጋ የሆነውን ሀብታችንን እንዳንጠቀም ስለሚፈልጉ እና አቅመ ቢስ ሆነን እንድንኖር ስለሚፈልጉ ነው ብለዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ነገ በአዲስ አበባ በልዩ ልዩ ክፍለ ከተሞች በወጣት ሊጉ አስተባባሪነት የተሰሩ የከተማ ግብርና ስራዎችን ተዘዋውሮ እንደሚጎበኝ ተጠቁሟል፡፡

በቅድስት ተስፋዬ፣ ተጨማሪ መረጃ ብልጽግና ፓርቲ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.