Fana: At a Speed of Life!

የብሔራዊ በጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልገሎት ሥልጠና በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ መሠጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 18 ፣ 2013  (ኤፍ.ቢ.ሲ)  በሀገር አቀፍ ደረጃ  የተዘጋጀው ብሔራዊ በጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልገሎት ሥልጠና በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ መሠጠት ተጀምሯል።

ለአርባ አምስት ቀናት በሚቆየው ስልጠና ላይ ለድሬዳዋና ከአዲስ አበባ ጨምሮ ከሁሉም ክልሎች የተወጣጡ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ 450 በጎ ፈቃደኞች እየተሳተፉ ነው።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት  ዶክተር ኡባህ አደም በሥልጠና መከፈቻ ላይ ÷ወጣቱ ሃገሪቱ ለጀመረችው የለውጥ ሂደት ስኬታማነት የማይተካ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡

ይህንን ታሳቢ በማድረግ ይህንን ሃይል በሀገራዊ የለውጥና የብልጽግና ጉዞ ውስጥ ተሳትፎውን ለማጠናከር ሥልጠናው ከፍተኛ  አስተዋጽኦ እንዳለው  የተናገሩት ዶክተር ኡባህ÷ የስልጠናው ተልዕኮ የተሳካ እንዲሆን ዩኒቨርስቲው አስተዋፅውን እንደሚያበረክት አረጋግጠዋል።

ስልጠናው በተጀመረበት ወቅት የሠላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል÷ ለሠልጣኞቹ የሥልጠናውን ዓላማ በተመለከተና ከስልጠናው በኋላ ከሰልጣኞች የሚጠበቀውን  ተግባር በቪዲዮ ኮንፍረንስ  መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሥልጠናውን  በሠላም ሚነስቴርና ዩኒቨርሲቲዎች የጋር ትብብር የተዘጋጀ መሆኑና ለአርባ አምስት ቀናት በሚቆየው ስልጠናም በብሄራዊ የበጎ ፍቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ላይ በቡድንና በጋራ እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በተሾመ ኃይሉ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.