Fana: At a Speed of Life!

የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት መርሃ ግብር ዓላማ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ስብዕና በማሳደግ ለመጭው ትውልድ በጎ አሻራ ጥሎ ማለፍ ነው – ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ወደ ተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ለገቡ የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ሰልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ሚኒስትሯ በቅርቡ ወደ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ዋቻሞ፣ ሰመራ፣ ድሬዳዋ፣ ድብረማርቆስና አምቦ ዩኒቨርስቲዎች ለገቡ በጎ ፈቃደኛ ሰልጣኞች ባስተላለፉት መልዕክት የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ወጣቶች ያለቸውን ዕምቅ ዕውቀት እና ችሎታ አውጥተው የሚጠቀሙበት እና ራሳቸውን ፈልገው የሚያገኙበት ነው ብለዋል፡፡
ይህ መርሃ ግብርም የበለፀገችና ሁለንተናዊ ሰላሟ የተረጋገጠባት ሀገር ለመገንባት ታስቦ የተጀመረ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሯ ከፕሮግራሙ ጋር ተያይዞ በአንዳንድ ግለሰቦች የተዛባ ወሬ ይወራል ይህም ዓላማውን ጠንቅቆ ካለመረዳት የመነጨ መሆኑን ለሰልጣኞቹ ገልፀዋል፡፡
የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ዓላማ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ስብዕና በማሳደግ ለመጭው ትውልድ በጎ አሻራ ጥሎ ማለፍ ነው ብለዋል ፡፡
የሰላም ሚኒስቴርም የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ሰልጣኞች ማህበረሰቡን በተለያዩ ዘርፎች ካገለገሉ በኋላ በተለያዩ የስራ መስኮች እንዲሰማሩና የስራ ዕድል እንዲመቻችላቸው ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ እንደሚገኝም ወይዘሮ ሙፈሪሃት መግለፃቸውን ከሰላም ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.