Fana: At a Speed of Life!

የብር ኖት ላይ ለውጥ መደረጉ ኮንትሮባንድን ለመቀነስ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብር ኖት ላይ ለውጥ መደረጉ በብርም ሆነ በውጭ ሀገር ገንዘብ የሚደረገውን ኮንትሮባንድ ለመቀነስ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ።

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ከፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት፥ የብር ኖቱ ለውጥ በኮንትሮባንድ ይገቡ የነበሩ እና ህብረተሰቡን ለተለያዩ የጤና እና የደህንነት ችግር የሚየጋልጡ ህገውጥ ተግበራትን ይቀንሳል።

እንዲሁም የህገወጥ የገንዘብ ከምችት እና ዝውውር ወንጀሎኞች እንዳሻቸው ሀገር እንዳትረጋጋ እና ሰላም አንዳትሆን የሚያደርጉ ህገወጥ የጦር መሳርያዎቸ እንዲያስገቡ በር ከፍቶላቸው መቆየቱን አንስተዋል፡፡

በሌላ በኩልም ህብረተሰቡን ለተያየ የጤና ችግር የሚዳርጉ አደንዛዥ እጾች፣ ጊዜያቸው ያለፈባቸው የምግብ እና የመድሃኒት ምርቶች እንዲገቡ ምክንያት ሆኖ ቆይቷል።

ይህን ፈታኝ የሆነ ህገወጥ ተግባር ለመቆጣጠርም የብር ኖት ለውጡ ለኮሚሽኑ ከፍተኛ አቅም እንደሚፈጥርም ኮሚሽነሩ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

አጋጣሚውን በመጠቀም የብር ኖቱ ለውጥ ይፋ ከተደረገበት እለት ጀምሮ ኮሚሽኑ በተለይም በድንበር አካባቢዎች እና በሁሉም ኬላዎች ላይ ጠንከር ያለ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑንም ኮሚሽነር ደበሌ ገልጸዋል።

በዚህም ከወዲሁም ቀላል የማይባሉ ውጤቶች እየታዩ መሆኑን ያነሱት ኮሚሽነሩ፥ አስከ ትናንት ድረስም ከቶጎ ጫሌ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ የነበረ 200 ሺህ ብር፤ በአሶሳ በኩልም በተመሳሳይ ወደ ሀገር ወስጥ ሊገባ የነበረ ወደ 600 ሺህ ብር መያዝ መቻሉን ተናግረዋል።

በትእግስት አብርሃም
#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.