Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ የትምህርት ተቋማት በዛሬው እለት በርካታ ተማሪዎችን አስመርቀዋል

 

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደብረማርቆስ፣እንጅባራ ዩንቭርስቲዎች እና ደሴ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በርካታ ተማሪዎች በዛሬው እለት አስመርቀዋል፡፡

የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያስተማራቸውን 2 ሽህ 905 በደማቅ ስነ-ስርዓት በቡሬ ካምፓስ አስመርቋል።

በተመሳሳይ እንጅባራ ዩኒቨርስቲ ለሁለተኛ ዙር 1 ሺህ 74 ተማሪዎችን ነው  በዛሬ እለት ያስመረቀው።

ዩኒቨርሲቲው የአዊኛ ቋንቋ እና ባህልን ለማሳደግ እየሠራ ይገኛል፡፡

በ2014 ዓ.ም አዊኛ ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ዲፖርትመንት ከፍቶ ለማስተማርም ዝግጅት ማጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ የምርቃት ዜና የደሴ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 457 ተማሪዎችን ዛሬ ያስመረቀ ሲሆን ተመራቃዎቹ በፋርማሲ፣ ሜዲካል ላብራቶሪ ጤና ኤክስቴንሽን እና በድንገተኛ ህክምና ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው::

ከተመራቂዎቹ መካከል 336 የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን ባልደረባችን  አንድነት ናሁሰናይ ዘግቧል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎች:-  ከአሚኮ እና ከኢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.