Fana: At a Speed of Life!

የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች በእስራኤል ኤምባሲዋን ከፈተች

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች በእስራል ቴል አቪቭ ኤምባሲዋን ከፈተች፡፡

ኤምባሲው ሃገራቱ የዲፕሎማሲ ግንኙነታቸውን ለማደስ ከተስማሙ ከአመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ነው የተከፈተው፡፡

በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱም ላይ አዲሱ የእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ እና በእስራኤል የኢሚሬቶች አምባሳደር ሞሐመድ አል-ካጃ ተገኝተዋል፡፡

የእስራኤል ፕሬዚዳንት ሄርዞግ ከአረብ ኢሚሬቶች ጋር የተደረገው ስምምነት ታሪካዊ እና ግንኙነቱም ከእስራኤል ጋር ሰላም ወደሚፈልጉ ሌሎች ሀገራት እንደሚሰፋ ነው የተናገሩት፡፡

በእስራኤል የኢሚሬቶች አምባሳደር አል-ካጃ በበኩላቸው የኤምባሲው መከፈት እያደገ ላለው የሃገራቱ ግንኙነት ትልቅ እመርታ ነው ብለዋል፡፡

እስራኤል ባለፈው ወር በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ኤምባሲዋን በይፋ መክፈቷን አልጀዚራ በዘገባው አስታውሷል፡፡

ኢሚሬቶች ለእስራኤል እውቅና የሰጠች አረብ ሀገር ስትሆን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ኢኮኖሚያዊ ግንኙነትም መጠናከሩን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ምንጭ÷አልጀዚራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.