Fana: At a Speed of Life!

የተጀመረው የሪፎርም ሥራ የሕገመንግስት የበላይነትና ሕገ መንግስታዊ ስርዓትን በተሻለ ለማስፈጸም ይረዳል – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የተጀመረው የሪፎርም ሥራ የሕገ መንግስት የበላይነትና ሕገ መንግስታዊ ስርዓትን በተሻለ ለማስፈጸም እንደሚረዳ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ፡፡

አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ ይህንን ያሉት የፌዴራል፣ የክልልና ከተማ አስተዳድር ምክር ቤቶች የጋራ ምክክር መድረክ ላይ ነው፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የተጀመረው የሪፎርም ሥራ የሀገራዊ ሪፎርም አካል ሆኖ የምክር ቤቱን ተልዕኮ በተሻለ የሚያሳልጥ ተግባር መሆኑን ያነሱት አፈ ጉባኤው ሪፎርሙ ግልጽ ዓላማና ግብ ተቀምጦለት እሱን ለማሳካት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ነው ያስረዱት፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት ረዳት ፕሮፌሰር ዋቅቶሌ ዳዲ በበኩላቸው የሕግ ማዕቀፍ ክፍተቶችን መለየትና መሙላት፣ ግልጽ የአሰራርና የአደረጃጀት ስርዓት መዘርጋት፣ የምክር ቤቱን ስልጣንና ተግባር ቀልጣፋ፣ ውጤታማና በብዙኃኑ ዘንድ ቅቡልነት ያለው ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ሪፎርሙ አራት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ሲሆን እነሱም ሀገራዊ አንድነትንና ዘላቂ ሰላም መገንባት፣ ውጤታማ የፊስካል ሽግግርና ፍታዊ  የሀብት ክፍፍል ማረጋገጥ፣ የሕገ መንግስት የበላይነትና ሕገ መንግስታዊነትን ማረጋገጥ እና ተቋማዊ የማስፈፀም አቅም መገንባት ናቸው ተብሏል፡፡

ምክር ቤቱ በሕግ መንግሥቱ በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሠረት ሀገራዊ  ለውጡን ተከትሎ ዘርፈ ብዙ ለውጦችን እያደረገ እንደሚገኝ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.