Fana: At a Speed of Life!

የቱሪስት መዳረሻዎችን የማልማት ስራዎች ቱሪዝምን በማነቃቃት ሀገራዊ ምጣኔ ሀብት ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሁን ላይ የተጀመሩ የቱሪስት መዳረሻዎችን የማልማት ስራዎች ቱሪዝሙን በማነቃቃት ሀገራዊ ምጣኔ ሀብት ለማሳደግ የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የምጣኔ ሃብት ጉዳዮች መምህርና ተመራማሪ ዶክተር ንጉሴ ስሜ፥ አሁን ላይ የተጀመሩ የቱሪስት መዳረሻዎችን የማልማት እና የማሳደግ ስራዎች ኢንቨስትመንትን እንደሚያነቃቃ ገልጸዋል።

የተጀመሩ የቱሪስት መዳረሻዎችን የማልማት እና ማሳደግ ስራዎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ያነሱት ዶክተር ንጉሴ፥ በተለይ ስራዎቹ በሚሰሩበት አካቢዎች የሚፈጠረው የኢንቨስትመንት መነቃቃትን ተከትሎ የሚገኙ መልካም አጋጣሚዎችን በቀዳሚነት ተመልክተዋል።

ሌላኛው የምጣኔ ሃብት ባለሙያ እና ሶሾ ኢኮኖሚክ ጉዳዮች ተንታኝ ዋሲሁን በላይ እንዳሉት፥ ሃገር በቀል እውቀቶች ተግባራዊ የተደረጉበት እና የሃገሪቱን ማህበረ ፖለቲካ በአንድ ስፍራ ለማስጎብኘት አሁን ላይ የተደረገዉ ሙከራ የበርካቶችን ቀልብ እንዲስብ የሚያደርግ ነው።

በተጨማሪም ይህ የሀገርን ሃብት የሀገር ልጅን ባሳተፈ መልኩ የማልማት እንቅሰቃሴ፣ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ማጠናቀቅ እና ወደ ስራ ማስገባት እንደሚገባ ምሳሌ የሚሆን ነው ብለዋል።

አካባቢን እና ተፈጥሮን ከመንከባከብ ጋርም ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው የቱሪስት መዳረሻዎችን የማልማት እና ማሳደግ ስራ ፓርኪንግ ዴቨሎፕመንት፣ በዜጎች ጤናማ ህይዎት ላይ አወንታዊ ሚና እንዳለዉም ገልፀዋል።

እንዲሁም ባለሙያዎቹ መሰል ሀገራዊ ፕሮጀክቶች የመንግስትና ማህበረሰብን ግንኙነት ለማጠናከር ወሳኝ ሰለመሆናቸው ጥናቶችን ዋቢ አድርገዉ የተናገሩ ሲሆን፥ ህዝብ በመንግስት ላይ ያለውን አመኔታ ከፍ እንደሚያደርግም አንስተዋል።

በአወል አበራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.