Fana: At a Speed of Life!

የቱሪስት ጉብኝት ለማስጀመር በተዘጋጀ ፕሮቶኮል ዙርያ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በመጠንቀቅ የቱሪስት ጉብኝት ለማስጀመር በተዘጋጀ ፕሮቶኮል ዙርያ ውይይት ተካሄደ፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር  ውይይቱን ያካሄደው÷ከክልል ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ ከግል ሴክተር ባለሃብቶች፣ ከሆቴል ባለቤቶች እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ነው።

ወረርሽኙ በቱሪዝም ዘርፉ ላይ አስከትሎት የነበረውን ተጽዕኖ በመቅረፍ የዘርፉን እንቅስቃሴ ለማስጀመር በተዘጋጀው ፕሮቶኮል ዙርያ ውይይቱ ማተኮሩ ተገልጻል፡፡

የኢፌዲሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚንስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ÷የቀረበው የፕሮቶኮል ሰነድ በዓለም ጤና ድርጅት እና በአፍሪካ በሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል መመሪያዎች እና ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በሚሰጡ ምክረ ሃሳቦች የሚመራ እና የሚተገበር መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ይህ መመሪያ በጥብቅ ተግባራዊ እንዲደረግ በሆቴል ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች እና ተቋማት መዘጋጀት እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል በተቀናጀ  እና በተናበበ መልኩ ክትትል እንዲሁም ድጋፍ እንደሚያደረግም ሚኒስትሯ  አክለው መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡፡፡

በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት የተዘጋውን የቱሪዝም ኢንደስትሪ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ለመክፈት እቅድ መያዙን በቅርቡ መገለጹ ይታወሳል፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.