Fana: At a Speed of Life!

የቱርክ ዩክሬንንና ሩሲያን የማደራደር ፍላጎት በሁለቱም ወገኖች ዘንድ ተቀባይነት ማግኘቱን አንካራ ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዩክሬንና ሩሲያ መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ቱርክ ያሳየችው የአደራዳሪነት ሚና በሁለቱም ወገኖች ዘንድ ተቀባይነት ማግኘቱን አንካራ ገለፀች።

የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን የተገኙበትና በወቅታዊ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ግኑኝነት ጉዳዮች ላይ አተኩሮ በተካሄደ የገዢው ፓርቲ (ኤ ኬ) ስብሰባ ላይ እንደተገለፀው፥ ቱርክ በዩክሬንና ሩሲያ መካከል እየጠነከረ የመጣውን ውጥረት ለማርገብ ያሳየችውን የአደራዳሪነት ሚና ሁለቱም ወገኖች መቀበላቸው ተመልክቷል።

በመሆኑም ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን ወደ ዩክሬን እንደሚያቀኑ ነው የተመለከተው። በመቀጠልም ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላደሚር ፑቲን ጋር ተገናኝተው ይወያያሉ ተብሏል።

የቱርክ ፍላጎት አሁን የተፈጠረውን ውጥረት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ማርገብ መሆኑን የገለፁት የፓርቲው ቃል አቀባይ ኦማር ሴሊክ፥ አሁን ላይ የጥቁር ባህር አካባቢ ሌላ ውጥረት እና ግጭት ውስጥ መግባት የለበትም ብላ ሀገራቸው እንደምታምን ተናግረዋል።

ሩሲያ ከ100 ሺህ የሚልቁ ወታደሮቿን፣ ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎቿንና ታንኮቿን ወደ ዩክሬን ድንበር በማስጠጋት ለወረራ እየተዘጋጀች ነው በሚል ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ አንዳንድ ምእራባውያን ሀገራት ከሞስኮ ጋር ወደ ተካረረ ውዝግብ ውስጥ ገብትዋል።

ሆኖም ሩሲያ ወታደሮቿ በመደበኛ የልምምድ ተግባር ላይ መሆናቸውን በመጥቀስ የዩክሬንንና የሌሎችን ምእራባውያን ሀገራት ክስን እንደምታጣጥል የቱርክ የዜና ወኪል (አናዱሉ) ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.