Fana: At a Speed of Life!

የቱኒዚያ አዲሱ መንግስት የመተማመኛ ድምጽ አገኘ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱኒዚያ አዲሱ መንግስት በፓርላማው የመተማመኛ ድምጽ አገኘ።

ፓርላማው ባለፈው ወር ማብቂያ ላይ በሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ካይስ ሳይድ የቀረበውን የኤልዬስ ፋክህፋክህን ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመትም አጽድቆታል።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመሰረተው ጥምር መንግስትም በፓርላማው የመተማመኛ ድምጽ ማግኘቱ ተገልጿል።

በቀድሞው የገንዘብ ሚኒስትር የሚመራው መንግስት በ129 ድጋፍ እና በ77 ተቃውሞ ይሁንታን አግኝቷል።

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርም የቱኒዚያን ኢኮኖሚ እንዲያገግም ማድረግ እና ሥራ አጥነትን መቅረፍ ቀዳሚ ተግባራቸው ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ france24.com/

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.