Fana: At a Speed of Life!

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የሚመሩበትን ፖሊሲና ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 24 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የሚመሩበትን አዲስ ፖሊሲና ስትራቴጂ ሰነድ ይፋ ሆነ።
ለአገራዊ ብልጽግና እውን መሆን ለቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተቋማቱ የሚመሩበትን አዲስ የፖሊሲና ስትራቴጂ ሰነድ ለባለድርሻ አካላት ይፋ አድርጓል።
በአገሪቱ በመንግስትና በግል ዘርፍ 1 ሺህ 600 የዘርፉ ተቋማት ቢኖሩም የጠራ ፖሊሲና ስትራተጂ ባለመኖሩ የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ እንዳላበረከቱ በመድረኩ ተመላክቷል።
የዘርፉን ችግር በዘላቂነት በመፍታት ተቋማቱ ለአገር ኢኮኖሚ ግንባታ ማበርከት ያለባቸውን አስተዋጽኦ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የፖሊሲው ትግበራ ማስፈለጉ ተገልጿል።
በመሆኑም ፖሊሲና ስትራተጂው አግባብነት፣ ጥራት፣ ተደራሽነትና ፍትሃዊነት፣ የፈጠራና የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የሳይንስ እና ባህል ግንባታ፣ መሰረተ ልማት እና የሰው ሃይል ግንባታ የሚሉትን ጉዳዮች ዋና ዋና ቁልፍ ተግባራት ማድረጉ ተገልጿል።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በወቅቱ እንደገለጹት÷ ዘርፉ ለአጠቃላይ አገራዊ የብለጽግና ጉዞ የሚያበረክተው ሚና የላቀ ነው።
ከዚህ ቀደም የነበሩት አሰራሮች በቴክኖሎጂ የተደገፉ ባለመሆናቸው አመርቂ ውጤት እንዳልመጣ ገልጸው÷“ሰነዱ ለጥራት፣ አግባብነትና ቴክኖሎጂው ትኩረት ሰጥቷል” ብለዋል።
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ከዚህ በፊት በነበረው አሰራር የዘርፉ ፖሊሲና ስትራተጂ ከሚወጡ ዕቅዶች ጋር እንደማይናበቡ አስታውሰዋል።
የአሁኑ ሰነድ ይህንን ችግሩን እንደሚፈታና ውጤት እንደሚመጣ ያላቸውን ተስፋ ተናግረዋል።
የቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ስልጠና ዘርፍ ዳይሬክተር ጄነራል ዶክተር ገነነ አበበ በበኩላቸው ÷ሰነዱ በተቀመጠለት አቅጣጫ ከተተገበረ የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.