Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት መረጃና አስተዳደር ስርዓትን ለማሻሻል እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትምህርት መረጃና አስተዳር ሥርዓትን ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የሚኒስቴሩ የትምህርት መረጃና አስተዳደር ስርዓት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ሰብስብ ለማ እንዳሉት÷ የሚኒስቴሩ የትምህርት መረጃ ስርዓት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እቅዶች ጋር በተናበበ መልኩ የመረጃ መሰብሰቢያ ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል የመረጃ መሰብሰቢያ ቋት ማሻሻያ በባለሙያዎች እየተዘጋጀ ነው፡፡
የሚሻሻለው የትምህርት መረጃ መሰብሰቢያ የነበሩትን በማስተካከልና አዳዲስ አሳቤዎችን በማካተት የሚዘጋጅ መሆኑም ታውቋል፡፡
እየተሰራ ባለው ማሻሻያ ላይም ከትምህርት ሚኒስቴርና ከሁሉም ክልል ትምህርት ቢሮ የተውጣጡ የትምህርት መረጃና አስተዳደር ስርዓት ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛል፡፡
የሚሻሻለው የመረጃ መሰብሰቢያ ስርዓት እንደ ትምህርት ዘርፍ የሚስተዋለውን የመረጃ ስርዓት ችግር ይፈታል ተብሎ እንደታመነበት ከትምህር ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.