Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ሚኒስቴር የሚያስተባብረው ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር የሚያስተባብረው ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ዛሬ ተጀምሯል።

በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ በሁሉም ደረጃ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና የትምህርቱ ማህበረሰብ አማካኝነት የሚከናወነው ይህ መርሀ ግብር 500 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል እቅድ የያዘ ነው ተብሏል።

እስከ ሃምሌ 30 በመከናወነው በዚህ መርሀ ግብር አንድ ተማሪ 40 ችግኞችን፤ አንድ መምህር ደግሞ 60 ችግኞችን በመትከል የታሰበውን እቅድ ለማሳካት ይሰራል ተብሏል።

ዛሬ በአዲስ አበባ መድሃኒዓለም መሰናዶ ትምህርት ቤት በተከናወነው የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ላይ የታደሙት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ወይዘሮ ሁሬያ አሊ፥ የአረንጓዴ አሻራን ወደ ትምህርት ቤት ግቢ ማምጣት ሀገር ተረካቢ ታዳጊዎች ከተፈጥሮ ጋር ተዋውቀው እንዲያድጉ ያስችላቸዋል ብለዋል።

ለዚህ መርሀ ገብር መሳካትም ሁሉም የትምህርት ዘርፍ ማህበረሰብ ርእርብ እንዲያደርግም ጠይቀዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የዛሬው ቀን በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የአረንጋዴ አሻራ ቀን ብሎ በመሰየም ነው በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የችግኝ ተከላ ማከናወን የጀመረው።

በመርሃ ግብሩ ላይ ከ4ኛ ክፍል በላይ የሚገኙ ተማሪዎች፤ ሁሉም መምህራን እና የአስተዳደር ስራተኞች እንደሚሳተፉ ታውቋል።

ይህ ተግባርም በቋሚነት በየዓመቱ ሰኔ 30 አጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ አንዱ ተግባር አረንጓዴ አሻራን የማሳረፍ ቀን ሆኖ እንዲከበር መወሰኑንም ሚኒስቴሩ አስታወቀ።

በዘመን በየነ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.