Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ስርዓቱን ሃገር ገንቢ ለማድረግ ቁርጠኞች ነን-ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ስርዓቱን ሃገር ገንቢ ለማድረግ ቁርጠኞች ነን ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እርስ በእርስ እንዳንተማመን ያደረገን ስርዓት ጊዜው አብቅቶ “ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም” ለማድረስ በሙሉ አቅማችን ወደ ስራ የምንገባበት ጊዜ ተቃርቧል ብለዋል።

የትምህርት ስርአቱን ሃገር ገንቢ ለማድረግ ቁርጠኞች ነን ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ወደ ግንባር ለሚዘምቱ ከትምህርት ሚኒስቴርና ከተጠሪ ተቋማት ለተውጣጡ በጎ ፍቃደኛ ዘማቾች ሽኝት በተደረገላቸው ወቅት ነው፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ÷ በቀጣይ አመታት ኢትዮጵያ የተሻለች እና ጠንካራ መሆን እንድትችል በትኩረት መስራት ይኖርብናል ሲሉ ተናግረዋል።

በመድረኩ ለመከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ ተደርጓል፡፡

በይስማው አደራው ተጨማሪ መረጃ የትምህርት ሚኒስቴር

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.