Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ቤቶችን ዝግጁነት የሚያጣራ ኮሚቴ ወደ ስራ ገባ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ቤቶችን ዝግጁነት የሚያጣራ ኮሚቴ ወደ ስራ መግባቱ ተገለፀ፡፡
የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ትምህርት ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አስታውቀዋል።
በዚህም የትምህርት ቤቶችን ዝግጁነት ለማረጋገጥ ከጤና ፣ ከትምህርት ፣ ከአስተዳደር ዘርፍ እንዲሁም ከወላጆች የተውጣጣ ኮሚቴ መዋቀሩን እና ኮሚቴውም ስራዎችን በባለቤትነት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
የተዋቀረው ኮሚቴ በሚቀጥሉት ሶስት ሳምንታት ውስጥ ከትምህርት ሚኒስቴር የሚላኩ ቁሳቁሶች መድረሳቸውን የሚያጣራ ፣ ሌሎች ድጋፎችን የሚያስተባብር ፣ በትምህርት ቤቶች አስፈላጊው ግብዕቶች መኖራቸውን የሚመለከት፣ያሉበትን ሁኔታ እንዲሁም ትምህርት ቤቱ በአጠቃላይ ትምህርት ማስኬድ የሚችልበት ሁኔታ ላይ ስለመሆኑ ይገመግማል ብለዋል፡፡
የተዋቀረው ኮሚቴም የትምህርት ቤቶችን ነባራዊ ሁኔታ ገምግሞ ውሳኔ ሲያስልፍ ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱ ሲሆን ÷ትምህርት ቤቶችን የመክፈት ሁኔታም የሚወሰነው ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቹን ለመቀበል የሚያስችል ዝግጁነቱ ሲኖር መሆኑ ተነግሯል፡፡
በግል ትምህርት ቤቶችም የወላጅ ኮሚቴዎች የትምህርት ቤቱን ዝግጁነት ካላረጋገጡ እና ካላመኑበት ትምህርት ቤቱ ትምህርት መጀመር እንደማይችል ሚኒስትሩ መግለፃቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.