Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ህዝብ ህግ ለማስከበር በተደረገው ዘመቻ ላደረገው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ኮሚሽኑ ምስጋና አቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጁንታው አመራሮች በውጊያ ከተሸነፉ በኋላ ራሳቸውን ካለባበስ ጀምሮ በመቀያየር ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ እንዳሉ ፖሊስ መረጃው እንደደረሰው ገለፀ።

ያልተያዙትን ተፈላጊዎች ከተደበቁበት ቦታ ይዞ ለህግ ለማቅረብ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ህዝብ ከፖሊስ አባላት ጎን በመቆም እና አስፈላጊውን ጥቆማ በመስጠት የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣም ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በሀገር ክህደት ወንጀል ተጠርጥረው መያዣ ትዕዛዝ ወጥቶባቸው በቁጥጥር ስር የዋሉ አመራሮችና የጦር መኮንኖች ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑም ገልጿል።

በተለያዩ ጊዜያት በሀገር ክህደት ወንጀል ተጠርጥረው መያዣ ትዕዛዝ ካወጣባቸው አመራሮችና የጦር መኮንኖች መካከል በቁጥጥር ስር በዋሉት ምርመራ እያካሄደባቸው መሆኑንም ነው ያስታወቀው፡፡

የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በሚያካሄዱት የህግ ማስከበር ዘመቻ በጁንታው የህወሓት ቡድን ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመሳተፍ የጥፋት ስራው አካል ናቸው ብሎ በጠረጠራቸው ከ300 በላይ ከፍተኛ አመራሮችና የጦር መኮንኖች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ከፍርድ ቤት መውጣቱ ይታወቃል፡፡

በዚህም እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ከፍተኛ መኮንኖች መካከል፡-

  1. ሜ/ጀኔራል ገ/መድህን ፈቃዱ ሀይሉ
  2. ሜ/ጀኔራል ይዳው ገ/መድህን
  3. ብ/ጀኔራል ገ/ህይወት ሲስኖስ ገብሩ
  4. ብ/ጄኔራል ኢንሱ እጃጆ እራሾ
  5. ብ/ጄኔራል ፍስሃ ገ/ስላሴ
  6. ኮ/ል ደሳለኝ አበበ ተስፋዬ
  7. ኮ/ል እያሱ ነጋሽ ተሰማ
  8. ኮ/ል መብራቱ ተድላ ወ/ሚካኤል
  9. ኮ/ል ባራኪ ጠማሎው ገብሩ
  10. ኮ/ል ሀይላይ መዝገብ ማሾ
  11. ኮ/ል ፍሰኃ ግደይ ወ/ማርያም
  12. ሌ/ኮ/ል ሙዘይ ተሰማ ስዩም
  13. ሌ/ኮ/ል ፍሰሃ በየነ ገ/ኪዳን
  14. ሌ/ኮ/ል ምሩጽ ወ/አረጋይ ገ/መስቀል
  15. ሌ/ኮ/ል ምሩጽ በርሄ አበራ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸዉ ይገኛል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለም የመያዣ ትዕዛዝ ከወጣባቸው 81 የህወሀት ከፍተኛ አመራሮች ውስጥ ዶክተር አዲስአለም ባሌማ የተያዘ መሆኑ ይታወቃል::

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሀገር መከላከያ እና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ባካሄዱት የተቀናጀ የህግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት በተካሄደው የምርመራ ስራ እንደተጣራው እርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል፡-

  1. ኮ/ል ተስፋዬ ገ/መድህን
  2. ኮ/ል የማነ ገ/ሚካኤል
  3. ሌ/ኮ/ል ሀዲሽ ገ/ጻዲቅ
  4. ኮ/ል ማዕሾ
  5. ኮ/ል አለም ገ/መድህን የተባሉት እንደሚገኙበት ተረጋግጧል፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከሌሎች የፀጥታ ሀይሎች ጋር በመቀናጀት ቀሪ ያልተያዙ የጦር መኮንኖችንና የህወሀት አመራሮችን ከየተደበቁበት ጥሻ፣ ዋሻ እና የሀይማኖት ስፍራዎች በማደንና በመልቀም ለህግ ለማቅረብ እየሰራ እንደሚገኝ ነው የገለፀው፡፡

የጁንታው የህወሀት አመራሮች በውጊያ ከተሸነፉ በኃላ ራሳቸውን ካለባበስ ጀምሮ በመቀያየር ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ እንዳሉ ፖሊስ መረጃው ደርሶታል ብሏል ኮሚሽኑ፡፡

የትግራይ ክልል ህዝብ ህግ ለማስከበር በተደረገው ዘመቻ እስከዛሬ ላደረገው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ኮሚሽኑ ምስጋና እያቀረበ ያልተያዙትን ተፈላጊዎች ከተደበቁበት ቦታ ይዞ ለህግ ለማቅረብ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ከፖሊስ አባላት ጎን በመቆም እና አስፈላጊውን ጥቆማ በመስጠት የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ ኮሚሽኑ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳ

የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.