Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የስራ አፈጻጸም የውይይት መድረክ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ላለፉት ሶሰት ቀናት በመቐለ ከተማ ሲያካሂድ የቆየው የስራ አፈጻጸም የውይይት መድረክ ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ አጠናቀቀ።

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሰራ አስፈጻሚ ዶክተር አብረሃም በላይ በተገኙበት የተካሄደው መድረክ፥ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ባለፉት ጊዜያት ባከናወናቸው ስራዎች ዙሪያ ተወያይቷል።

በክልሉ የጸጥታ ሁኔታ፣ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሰብአዊ እርዳታና በመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሳጣጥ እንዲሁም በኮሮና ቫይረስ መከላከል ላይ ስለተከናወኑት ተግባራት በውይይቱ ከተነሱት ጉዳዮች መካከል ይገኙበታል።
ጊዜያዊ አስተዳደሩ በቀጣይ ወራት ትኩረት ሰጥቶ ስለሚያከናውናቸው ስራዎችም አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ትምህርት፣ ጤና ፣ ግብርናና ሌሎችንም የስራ ዘርፎች ወደነበሩበት ለመመለስ በመድረኩ ተሳታፊዎች የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

በተለይም መደበኛ ትምህርትን የተገኘውን አማራጭ ሁሉ በመጠቀም ለማስጀመር፥ በጤናው ዘርፍም ከመንግስትና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር አገልግሎቱን ለማጠናከርም መግባባት ላይ መደረሱን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።

በመድረኩ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የቢሮ ኃላፊዎችና የዞን አመራሮች ተሳትፈዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.