Fana: At a Speed of Life!

የቶኪዮ ኦሊምፒክ 2020 ዝግጅትን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ዝግጅትን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሄደ።

በመድረኩ ላይ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ዝግጅትን አስመልክቶ የመነሻ ሰነድ፣ ለቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ስለ ስፖርት ህክምና እና የፀረ አበረታች ቅመሞች ቁጥጥርና ክትትል ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

ከመድረኩ ተሳታፊዎችም የተለያየ ሃሳብና አስተያየት ቀርቦ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።

የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጂሎ፥ ውድድሩ ከቀረው ጊዜ አንጻር ለዝግጅቱ መሳካት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

የምክክር መድረኩ የአቋም መግለጫ በማውጣት መጠናቀቁን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.