Fana: At a Speed of Life!

የቻይናው ሲልክ ሮድ ሆስፒታል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት አገልግሎት እንዲሰጥ ተወሰነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 21 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው ሲልክ ሮድ ሆስፒታል ህክምና መስጫው ሙሉ በሙሉ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት አገልግሎት እንዲሰጥ ወሰነ።

የሆስፒታሉ አስተዳደር በዛሬው እለት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ለተቋቋመው ለብሄራዊ የህክምና እና ለይቶ ማቆያ ተቋማት ዝግጅት አስተባባሪ ኮሚቴ ሆስፒታሉን አስረክቧል።

በዚህ ወቅትም ለህክምና መስጫ የሚሆኑ 15 አልጋዎችን በጊዜያዊነት ያዘጋጀ ሲሆን፥ ሁኔታው እየታየ የአልጋው ቁጥር እንደሚጨምርም አስታውቋል።

በሆስፒታሉ ውስጥ የህክምና ክትትል ሲደረግላቸው የቆዩ ታካሚዎችን ወደ ሌላ ስፍራ ማዛወሩንም ገልጿል።

በርክክብ ስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ መሰል ጥረቶች ተጠናክረው መቀጠላቸው አስደሳች መሆኑን ገልጸዋል።

የተደረገው ድጋፍ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት ያግዛልም ነው ያሉት።

በሃብታሙ ተክለስላሴ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.