Fana: At a Speed of Life!

የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ እና የአሜሪካ አቻቸው ጆ ባይደን ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ እና የአሜሪካ አቻቸው ጆ ባይደን ከ7 ወራት ቆይታ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በስልክ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ሀገራቱ በቀጣይ የሚኖራቸውን ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
በተለይም በንግድ እና ሌሎች ዘርፎች ዙሪያ በሀገራቱ መካከል የሚስተዋሉ ውድድሮች ወደ ግጭት እንዳያመሩ በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ በትኩረት መምከራቸው ነው የተገለጸው፡፡
ሁለቱ ሃያላን ሀገራት ባለፉት ሰባት ወራት ውስጥ ከንግድ እና ከኮሮና ቫይረስ አመጣጥ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ ገብተው ቆይተዋል፡፡
አሁን ላይ ሁሉቱ መሪዎች ያደረጉት ውይይትም ሀገራቱ በንግድ፣ በሰብዓዊ መብት አያያዝና በኮሮና ቫይረሰ አመጣጥ ዙሪያ ገብተውበት የነበረውን እሰጣ ገባ እንደሚያረግበው ታምኖበታል፡፡

ምንጭ ÷ አልጀዚራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.