Fana: At a Speed of Life!

የቻይና ተመራማሪዎች ከ10 ሺህ በላይ በሊቲየም የበለጸጉ ከዋክብቶችን አገኙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና የስነ ፈለክ ተመራማሪዎች ከ10 ሺህ በላይ በሊቲየም ማዕድን የበለጸጉ ከዋክብቶችን ማግኘታቸውን ይፋ አደረጉ።

ይህም ከዚህ በፊት በዓለም ዙሪያ በህዋ ላይ ጥናት የሚያደርጉ ተመራማሪዎች ካገኟቸው መሰል ከዋክብቶች ቁጥር ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ነው ተብሏል።

ከዋክብቶቹ በቻይና ሳይንስ አካዳሚ የብሄራዊ ስነ ፈለክ ተመራማሪዎች ትልቅ የእይታ አቅም ያለውን ፋይበር ስፔክትሮስኮፒክ ቴሌስኮፕ በመጠቀም የተገኙ መሆኑ ተገልጿል።

ምርምሩ በሰሜናዊ ቻይና ሄብይ ግዛት ሺንግሎንግ በሚገኘው የስነ ፈለክ ምርምር ማዕከል ላይ ነው የተካሄደው።

አዲሱ ግኝት ተመራማሪዎች በሊቲየም የበለጸጉ ግዙፍ ከዋክብቶችን ሁለንተናዊ ገጽታ በጥሩ ሁኔታ ለመረዳት እና በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ያደርጋል ነው የተባለው።

ከዚህ ባለፈም ጥናቱ የከዋክብቶችን ዝግመተ ለውጥ እና ውስጣዊ አወቃቀር ሁኔታ በጥልቀት ለመረዳት እንደሚያስችል ታምኖበታል።

ምንጭ፦ ሺንዋ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.