Fana: At a Speed of Life!

የቻይና-አፍሪካ አጋርነት ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ የሚጠቅም ነው – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና- አፍሪካ አጋርነት ከቻይና እና ከአፍሪካ ድንበር አልፎ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ የሚጠቅም ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡

አቶ ደመቀ የቻይና አፍሪካ ትብብር መድረክ አስተባባሪዎች ስብሰባ ላይ በበይነ መረብ ተሳትፈዋል፡፡

የስብሰባው አላማም በፈረንጆቹ 2021 ህዳር ወር በሴኔጋል ዳካር የተካሄደው 8ኛው የቻይና-አፍሪካ የትብብር ፎረም የሚኒስትሮች ስብሰባ አላማ ውጤቶችና የአፈፃፀም ሂደት መገምገም መሆኑ ተገልጿል።

በበይነ መረብ በተካሄደው በዚሁ ስብሰባ ላይ የተሳተፉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ባደረጉት ንግግር÷ የቻይና አፍሪካ አጋርነት በአለም አቀፍ አስተዳደር፣ ዲፕሎማሲ እና ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረው በጎ ተፅዕኖ ከቻይና እና አፍሪካ አልፎ መላውን የአለም ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ብለዋል።

የቻይና-አፍሪካ የትብብር ፎረም የድርጊት መርሃ ግብር የአሁኑን ዓለም አቀፋዊ እድገቶች ተጽእኖ ግምት ውስጥ ማስገባት አለበት ነው ያሉት፡፡

በቻይና-አፍሪካ የትብብር ፎረም የሚኒስትሮች ስብሰባ አንዳንድ መርሃ ግብሮች አፋጣኝ ትኩረትና እርምጃ የሚሹ መሆናቸውንም አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

እንዲሁም ቻይና በአፍሪካ ቀንድ የሰላም፣ የጸጥታ፣ የአስተዳደር እና የልማት ኮንፈረንስ በማዘጋጀቷ አድናቆታቸውን ገልፀው፥ የጉባኤውን ውጤት ተግባራዊ ለማድረግ ኢትዮጵያ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.