Fana: At a Speed of Life!

የቼልሲው ተከላካይ አንቶኒዮ ሩዲገር የ11 ሴራሊዮናውያን ህፃናትን የቀዶ ጥገና ህክምና ወጪ ሸፈነ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 11 ሴራሊዮናውያን ህፃናት በቼልሲው ተከላካይ አንቶኒዮ ሩዲገር ወጪያቸው ተሸፍኖ የቀዶ ጥገና ህክምና ተደረገላቸው፡፡

በተጫዋቹ ወጪያቸው ተሸፍኖ የቀዶ ጥገና ህክምና የተደረገላቸው ህፃናት የከንፈር መሰንጠቅ፣ በቃጠሎ የተጎዱ እና በሰውነት አካላቸው ላይ የቅርፅ ችግር የነበረባቸው ህፃናት ናቸው፡፡

ከሴራሊዮናዊት እናት የተወለደው እና ለጀመርን ብሄራዊ ቡድን የሚጫወተው ሩዲገር ለእናት ሀገሩ ውለታ መዋሉ እንዳስደሰተው ተናግሯል፡፡

መነሻየ የሆነችውን ሴራሊዮን አደንቃለሁ ያለው አንቶኒዬ ሩዲገር፥ ከቢግሹ ጋር በመተባበር ድጋፍ በማድረጌ ደስተኛ ነኝ ብሏል፡፡

የቀዶ ጥገና ህክምና ሂደቱ መልካም እንደነበረ ባለፈው ሳምንት ከህክምና ቡድኑ መልዕክት እንደደረሰው በመግለፅ ለቡድኑ አባላት ምስጋና አቅርቧል፡፡

ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲ ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.