Fana: At a Speed of Life!

የኔዘርላንድስ መንግስት 67 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የኮቪድ19 የመከላከያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኔዘርላንድስ መንግስት ካርድ ኤይድ ከተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር 67 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ኮቪድ19ን ለመከላከልና ለማከም የሚያገለግል ግብዓት ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ፡፡
 
ድጋፉን የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ ተረክበውታል፡፡
 
ዶክተር ደረጀ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው ድጋፉ በቀላሉ በገበያ የማይገኙና ኮቪድን ለማከም የሚያገለግሉ ፀረ ባክቴሪያ መድሀኒቶችን ያካተተ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
 
ድጋፉ የህፃናት፣ የወጣቶችና የአዋቂዎች ማስክ፣ ጓንት፣ ሳኒታይዘር፣ መድሀኒቶች፣ ፈሳሽ ሳሙናና ፀረ ባክቴሪያ መድሃኒቶችን ያካተተ መሆኑን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በተያያዘ ዜና መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው ጄነራል ኤሌክትሪክ አጠቃላይ ግምታቸው 23 ሺሀ 244 የአሜሪካ ዶላር የሚያወጡ የፊት መሸፈኛ ጭምብሎችን ለጤና ሚኒስቴር አስረክቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.