Fana: At a Speed of Life!

የንግድ አውሮፕላን በረራ 42 በመቶ ቢቀነስም በአውሮፕላን አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም አቀፍ ደረጃ በፈረንጆቹ 2020 በንግድ አውሮፕላን አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።

ምንም እንኳን በኮሮና ቫይረስ ወረረሽኝ ምክንያት የንግድ አውሮፕላን በረራ በብዛት የተቋረጠ ቢሆንም በአውሮፕላን አደጋዎች የበርካታ ሰው ህይወት ማለፉ ነው የተነገረው።

በፈረንጀቹ 2020 በአውሮፕላን አደጋ የ299 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በ2019 ከነበረው የ257 ሰዎች ሞት ብልጫ አሳይቷል።

በወረርሽኙ ስርጭት ምክንያት በርካታ ገደቦች በታጣሉበት ወቅት በአደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከፍ ማለቱን ነው የኔዘርላንድስ አቪዬሽን አማካሪ ቶ70 ያወጣው መረጃ ያሳየው።

በፈረንጆቹ 2020 በንግድ አውሮፕላን በረራ ላይ ለ24 ሰዓታት የተደረገ ክትትል እንዳሳየው የበረራ መጠኑ በ42 በመቶ መቀነሱ ተነግሯል።

ይህ አሃዝ በትልልቅ የመንገደኞች አውሮፕላኖች ላይ የደረሰውን አደጋ ጨምሮ በረራ ላይ ተመተው የወደቁትን ይጨምራል ብሏል ቢቢሲ በዘገባው።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.