Fana: At a Speed of Life!

የንፁሃን ዜጎቻችንን ደም ማፍሰስ በቸልታ የማይታለፍ ነው – አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 25 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የንፁሃን ዜጎቻችንን ደም ማፍሰስ በቸልታ የማይታለፍ ነው አሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፡፡

አቶ ደስታ በሰጡት መግለጫ ህወሓት በመከላከያ ካምፕ ላይ የፈፀመው ጥቃት አሳፋሪ መሆኑን በማንሳት፤ የፖለቲካ ቁማርተኞች እጃቸውን ሊሰበስቡ ይገባል ብለዋል፡፡

የለውጡ ተቀናቃኞች በትግራይ ክልል ውስጥ በመከላከያ ካምፕ ያደረሰውን ጥቃት አውግዘዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ የለውጡ ተቀናቃኞች ስልጣንን በጉልበት ለመቆናጠጥ እያደረጉ ያሉትን እኩይ ተግባር ካላቆሙ ክልላቸው ሊመክት መዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡

ህወሓት ለ27 ዓመታት ህዝባችንን አፍኖ ቆይቷል ያሉት አቶ ደስታ፤ ዛሬም እኔ አለሁላችሁ ማለታቸው አግባብነት የለውም ብለዋል፡፡

የሲዳማ ህዝብ የጭቆናና የአፈና ስርአትን ተሻግሮ በለውጡ መንግስት ራሱን በራሱ ማስተዳደር የቻለ መንግስት ማቋቋሙን አስታውሰዋል፡፡

በያሬድ ጌታቸው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.