Fana: At a Speed of Life!

የአላውሃ ድልድይ በጎርፍ ምክንያት አደጋ ላይ መሆኑ ተገለፀ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በራያ ቆቦና ጉባላፍቶ ወረዳ ወሰን ላይ የሚገኘው የአላ ውሃ ድልድይ በክረምቱ ዝናብና ጎርፍ ምክንያት የመፍረስ አደጋ እንዳጋጠመው ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የራያ ቆቦ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮማንደር ነጋ ደንበሩ እንደገለፁት÷ ድልድዩ ከዚህ በፊት በአሸባሪው ትህነግ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት በመንግሥት ጥረት ጊዜያዊ የብረት ድልድይ ተሠርቶ አገልግሎት እየሰጠ ነበር፡፡

አሁን ላይ ከክረምቱ ጋር በተያያዘ በአካባቢው የዘነበውን ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ ጎርፍ ድልድዩ ከፍተኛ ጉዳት ስላጋጠመው፥ የሚመለከተው አካል አስቸኳይ ጥገና እንዲያደርግለት እና አገልግሎት የሚሰጥበት ሁኔታ እንዲመቻች ጠይቀዋል፡፡

ከዚህ በፊት ወደ ወረዳው የገቡት እና ሊገቡ ያሰቡ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ቢቆሙና ተጓዥ መንገደኞችም የጉዞ ሁኔታቸውን እንዲያስተካክሉ ማሳሰባቸውን የራያ ቆቦ ኩሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.