Fana: At a Speed of Life!

የአማራክልል ገቢዎች  የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ግብር ከፋዮች በባንክ በኩል ግብር እንዲከፍሉ አመቻቸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራክልል ገቢዎች ቢሮ የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ግብር ከፋዮች በባንክ በኩል ግብር እንዲከፍሉ አመቻቸ፡፡

የቢሮው  ሀላፊ ወይዘሮ ብዙአየሁ ቢያዝን   የነጋዴው  ማህበረሰብም  ከኮሮና ቫይረስ ለመጠበቅ  የባንክ መስኮት  አገልግሎት  ለመስጠት   በቢሮው  ውይይት  ተደርጎ ውሳኔ  ላይ መደረሱን  ገልፀዋል ፡፡

እንዲሁም  ሰራተኞችና የነጋዴዎች   ደህነት  ከኮሮና ቫይረስ  ለመጠበቅ   የግብር ስራውን  ለማስቀጠል  እየሰራ መሆኑን  ነው ያመለከቱት፡፡

ለዚህም የተቋሙ  3ዐ በመቶ የሚሆኑት ሰራተኞች ብቻ  በ6 ቡድን  ተከፍለው በእያንዳንዱ  ቡድን ሶስት ሶሰት ሙያተኞች  እንዲሰሩ  መደረጉን ሀላፊዋ ተናግረዋል፡፡

በዚህ አስቸጋሪ  ወቅት 124 ሚሊየን  ብር መሰብሰብ  መቻሉን  ወይዘሮ  ብዙአየሁ አንስተዋል፡፡

እንዲሁም የገቢዎች  ቢሮ ከሀምሌ 1 እሰከ መጋቢት  18 ቀን 2012   8 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ወይም ከአመቱ እቅድ  62 ነጥብ 4 በመቶ  መሰብሰብ  መቻሉን  አንስተዋል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.